ጤናማ ሆኖ መቆየት

ከታች የተጠቀሱትን ምክሮች ከተከተሉ ራስዎን ከብዙ ተላላፊ በሽታዎች መጠበቅ ይችላሉ፡፡

4a_Hände_waschen.png

ከተላላፊ በሽታ ራስን ለመጠበቅ በጣም ቀላሉ እና ውጤታማው መንገድ ሁልግዜ እና በደንብ እጅን በሳሙና መታጠብ መቻል ነው፡፡ ቢያንስ መፀዳጃ ቤት ደርሰው ከተመለሱ በኋላ እና ምግብ ከመመገብዎ በፊት ሁልግዜም እጅዎን ይታጠቡ፡፡

1d_Hände.png

ሁልግዜ ገላዎን ይታጠቡ እንዲሁም ጥርሶን በቀን ሶስት ግዜ ይቦርሹ፡፡

መደበኛ የሆነ የሰውነት ንፅህና መጠበቅ ከበሽታ ይጠብቆታል፡፡ የጥርስ ህመም ካለብዎ ሜዲክ-ኸልፕን ያግኙ፡፡

4d_Impfung.png

ብዙ በሽታዎችን በክትባት ማስወገድ ይቻላል፡፡ ሰዎች ብዙ በተከተቡ ቁጥር በትንሹ ይታመማሉ፡፡

የስዊዝ የጤና ባለስልጣን ለሚከተሉት ክትባትን ይመክራል (ጥቂቶቹን ለመግለፅ)

  • ጉድፍ
  • ኩፍኝ/ጆሮ ደግፍ/የጀርመን ኩፍኝ
  • ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ/ቴታነስ/ትክትክ
  • የልጅነት ልምሻ /ፖሊዮ
Icon_Medic_Help.png

ለምክር ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ

4e_Geschlechtsverkehr.png

ከኤድስ በተጨማሪ፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ብዙ በሽታዎች አሉ፡፡ በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ኮንዶምን በመጠቀም በጣም በተሻለ ሁኔታ ራስዎን መጠበቅ ይችላሉ፡፡ ለሴቶችም የሚሆን ኮንዶም አለ፡፡

በማእከሉ ውስጥ ኮንዶም ይሰራጫል ወይም ኬሚስቶች ፋርማሲ ውስጥ እና በአብዛኛዎቹ ሱፐር ማርኬቶች ውስጥ ይሸጣል፡፡

4f_Drogenkonsum.png

እፅ በሚወስዱበት ወቅት ጥቅም ላይ የዋለ መርፌ የሚጠቀሙ ከሆነ በደም አማካኝነት ለበሽታ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ሁልግዜም ንፁህ እና ጥቀም ላይ ያልዋለ መርፌ ይጠቀሙ፡፡

2c_Schwangerschaft.png

ነብሰ ጡር ከሆኑ ሜዲክ-ኸልፕን ያግኙ፡፡ ባለሙያው እርሶ እና ልጅዎ ጤናማ ሆናችሁ የምትቆዩበትን መንገድ ከእርሶ ጋር ቅድመ ሁኔታዎችን ይነጋገራል እንዲሁም ከህክምናው ልዩ ባለሙያ ጋር እንዲገናኙ ቀጠሮ ይይዛል፡፡

1b_Wo_medizinische_Hilfe.png

ልጆችዎን በመደበኛነት በሜዲክ-ኸልፕ እንዲታዩ ያድርጉ፡፡ ሜዲክ-ኸልፕ በልጅዎ የምግብ አጠቃቀም እና እንክብካቤ ዙሪያ ሊረዳዎ ይችላል፡፡ በዚህም የተነሳ ልጆችዎ ጤናማ ሆነው ይቆያሉ እና በተገቢው መንገድ ያድጋሉ ፡፡