Medic-Help Asyl
  • ቢታመሙ ምን ማድረግ እንዳለብዎ
    የበሽታ ምልክቶች
    በሽታዎች
    ጤናማ ሆኖ መቆየት
    የህክምና እንክብካቤ በስዊዘርላንድ
    የቅበላ መረጃ
    icon-sprache.png
    • English
    • Deutsch
    • Français
    • Italiano
    • Shqip (Albanisch)
    • Bamanakan (Bambara)
    • Fulani
    • Igbo
    • Hrvatski (Kroatisch)
    • Kurmancî
    • Lingala
    • Mandinŋo (Mandinka)
    • Português (Portugiesisch)
    • Română (Rumänisch)
    • Soomaali
    • Español
    • Kiswahili
    • Türkçe (Türkisch)
    • Twi
    • Wolof
    • العربية (al-Arabiya)
    • کوردی (Badini)
    • درى (Dari)
    • فارسى (Farsi)
    • پشتو (Paschtun)
    • پنجابی (Punjabi)
    • کوردیی ناوەڕاست (Sorani)
    • اردو (Urdu)
    • български (Bulgarisch)
    • Монгол (Mongolisch)
    • Українська (Ukrainisch)
    • русский (Russisch)
    • Հայերեն (Armenisch)
    • አማርኛ (Amharisch)
    • ትግርኛ (Tigrinnya)
    • ქართული (Georgian)
    • தமிழ் (Tamil)
    • བོད་སྐད (Tibetisch)
  • Für Betreuende:

  • የህግ ማስታወቂያ እና ግንኙነት

    ከዚህ ቀን ጀምሮ፡ ጃንዋሪ 2018

  • የበሽታ ምልክቶች
  • ሳል
  • ትኩሳት
  • የሌሊት ላብ
  • የቆዳ መቆጣት እና ማሳከክ
  • ክፍት ሆኖ በቆዳ ላይ የሚታይ ቁስል
  • ተቅማጥ
  • ማስመለስ
  • የመተኛት ችግር፣ ፍርሀት እና ህመም
  • ተጨማሪ ምልክቶች
Beschwerden.png

እዚህ በጣም አስፈላጊ ስለሆኑ የተላላፊ በሽታዎች ምልክቶች መረጃ እናቀርባለን፡፡  እነዚህን በአፋጣኝ ማከም አስፈላጊ ነው፡፡  ይህም ጤናዎን ይጠብቃል እንዲሁም ሌሎች በበሽታው እንዳይጠቁ ያደርጋል፡፡

Icon_Medic_Help.png

የትኛውም አይነት ምልክቶች ካሉብዎ ወይም ጤንነት ካልተሰማዎ ሜዲክ-ኸልፕን ያግኙ፡፡

Husten.png

ሳል የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ አብዛኛውን ግዜ ከጉንፋን ጋር ይያያዛል፡፡  አንዳንድ ጊዜ የተላላፊ በሽታዎች ማሳያ ነው፡፡

Icon_Medic_Help.png

ተከታታይ በሆነ እና ጠንካራ ሳል፣ ወይም ለረዥም ግዜ በቆየ ወይም አክታ ባለው ሳል እየተሰቃዩ ከሆነ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

ሳል የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል

ቲቢ

ኩፍኝ

Fieber.png

የሰውነት የሙቀት መጠን ከተለመደው በላይ ከሆነ ትኩሳት ተብሎ ይጠራል፡፡  የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

Icon_Medic_Help.png

ትኩሳት ካለብዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

Icon_Medic_Help.png

ልጅዎ ትኩሳት ካለበት በአፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

Icon_Trinken.png

በቂ ውሀ ወይም በአነስተኛ መጠን ሻይ ይጠጡ እንዲሁም አድካሚ የሆነ የሰውነት እንቅስቃሴን ያስወግዱ፡፡

ትኩሳት የተለያየ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡  ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል

ቲቢ

ጉድፍ

ኩፍኝ

Nachtschweiss.png

በሙቀታማ በጋ ሌሊቶች በጣም ማላብ የተለመደ ነገር ነው፡፡  ይህ የመኝታ ቤት ከመጠን በላይ ከሞቀም የሚከሰት ነው፡፡ ነገር ግን፣ መደበኛ የሙቀት መጠን ባለበት ክፍል ውስጥ ከመጠን በላይ የሚያልብዎ ከሆነ የተላላፊ በሽታ መያዝዎን ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡

Icon_Medic_Help.png

ከሌሊት ላቡ በተጨማሪ ትኩሳት ካለዎ እና ክብደት እየቀነሱ ከሆነ ወደ ሜዲክ ኸልፕ ይሂዱ፡፡

የሌሊት ላብ የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡  ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል

ቲቢ

Hautauschlag.png

በቆዳ መቆጣት ወቅት ቀይ ክብ ነጥብ ወይም ማንኮፍኮፍ በቆዳ ላይ ይታያል ወይም ቆዳው በጣም ይደርቅ እና ይሰነጣጠቃል ወይም በጣም ያሳክካል፡፡  ይህ የተላላፊ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

Icon_Medic_Help.png

ቆዳዎ ከተቆጣ ወይም ካሳከክዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

የቆዳ መቆጣት እና ማሳከክ የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል

በነብሳት ንክሻ የሚመጣ በሽታ

ጉድፍ

ኩፍኝ

Offene_Hautwunden.png

መቆረጦች፣ ጭረቶች፣ ወይም ንክሻዎች ቆዳን ሊጎዱ እና ቁስለት ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ በአግባቡ ያልዳነ ቁስል ልዩ አትኩሮትን ይፈልጋል፡፡

Icon_Medic_Help.png

ክፍት ሆኖ የሚታይ ቁስል ካለብዎ፤ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

ክፍት ሆኖ በቆዳ ላይ የሚታይ ቁስል ብዙውን ግዜ የጉዳት ምልክት ነው፡፡  በአግባቡ የማይድኑ ከሆነ፤ ይህ ማለት ምልክት ሊሆን ይችላል፡

ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ

Durchfall.png

በቀን ከሶስት ግዜ በላይ የአንጀት መታወክ ካጋጠምዎ ወይም ካስቀመጥዎ፤ ይህ ተቅማጥ ይባላል፡፡  ይህ የተላላፊ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

Icon_Medic_Help.png

ተቅማጥ ካለብዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

Icon_Trinken.png

በቂ ውሀ እና የተወሰነ መጠን ያለው ሻይ ይጠጡ፡፡

Icon_Haende_waschen.png

ሌሎችን መበከልን ለማስወገድ ሁልግዜም እጅዎን በሳሙና ይታጠቡ፡፡

ተቅማጥ የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡  ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል

የጨጓራ ህመም

Erbrechen.png

ማስመለስ የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ማስመለስ የተላላፊ በሽታዎች ምልክት ሊሆንም ይችላል፡፡

Icon_Medic_Help.png

የሚያስመልስዎ ከሆነ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

Icon_Trinken.png

በቂ ውሀ እና የተወሰነ መጠን ያለው ሻይ ይጠጡ፡፡

Icon_Haende_waschen.png

ሌሎችን መበከልን ለማስወገድ ሁልግዜም እጅዎን በሳሙና ይታጠቡ፡፡

ማስመለስ የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል

የጨጓራ ህመም

Schlechter_Schlaf.png

ለብዙ ሌሊቶች የመተኛት ችግር ካጋጠምዎ ወይም ማብራራት የማይችሉት አይነት ፍርሀት ይሰማዎ ከሆነ ይህ የአእምሮ ችግር ወይም ስቃይ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡  ይህ የሚታይ ምልክት ከሌለው ህመም ጋርም አብሮ ይሄዳል፡፡

Icon_Medic_Help.png

በአግባቡ እየተኙ ካልሆነ ወይም እንግዳ የሆነ ህመም ከተሰማዎ ሜዲክ-ኸልፕን ያግኙ፡፡

የመተኛት ችግር፣ ምክንያት አልባ ፍርሀት ወይም እንግዳ የሆነ ህመም የተላላፊ በሽታ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡  ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል፡ 

የስሜት/የአእምሮ ስቃይ

Weitere_Beschwerden_w.png

በዚህ ገፅ ላይ በዋነኛነት የሚያገኙት መረጃ ስለ በጣም አስፈላጊ ስለሆኑት ተላላፊ በሽታዎች ይሆናል፡፡ 

እርግጥ ነው፤ ብዙ አይነት ምልክቶች አሉ፡፡  ህመም ከተሰማዎት እና ጤና ነክ የሆነ ጥያቄ ካሎት ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

BAG-Logo-de EDI_BAG_e_RGB_pos_hoch.png
Datenschutzerklärung