በእያንዳንዱ የእንግዳ መቀበያ እና የሂደቱ ማዕከል ውስጥ የህክምና ባለሙያዎች (ሜዲክ-ኸልፕ) ይገኛሉ፡፡ መድሀኒት እየወሰዱ ከሆነ፣ ነብሰ ጡር ከሆኑ ፣ ህመም ከተሰማዎ ወይም ማንኛውም አይነት ከጤና ጋር የተያያዘ ጥያቄ ካሎት ቀርበው ያናግሯቸው፡፡ እነዚህ ባለሙያዎች ክህምና ይሰጥዎታል፤ እንደ አስፈላጊነቱም ወደ ዶክተር ወይም ወደ ሆፒታል ይልኮታል፡፡
ሜዲክ-ኸልፕ ዝግ ከሆነ፤ ለድጋፍ አደራጊው ወይም የጥበቃ ሰራተኛው ያመልክቱ፡፡
የእርሶ ጤና-ነክ ጥያቄዎች እና ስለ በሽታዎ የተመዘገበ መረጃ በሚስጥር እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡
እንዲሁም በአደጋ ግዜ በመጀመሪያ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡ ለድንገተኛ አደጋ ብቻ ሲሆን በቀጥታ ወደ ሆስፒታል ይሂዱ፡፡