ቢታመሙ ምን ማድረግ እንዳለብዎ

በእያንዳንዱ የእንግዳ መቀበያ እና የሂደቱ ማዕከል ውስጥ የህክምና ባለሙያዎች (ሜዲክ-ኸልፕ) ይገኛሉ፡፡  መድሀኒት እየወሰዱ ከሆነ፣ ነብሰ ጡር ከሆኑ ህመም ከተሰማዎ ወይም ማንኛውም አይነት ከጤና ጋር የተያያዘ ጥያቄ ካሎት ቀርበው ያናግሯቸው፡፡  እነዚህ ባለሙያዎች ክህምና ይሰጥዎታል፤ እንደ አስፈላጊነቱም ወደ ዶክተር ወይም ወደ ሆፒታል ይልኮታል፡፡ 

ሜዲክ-ኸልፕ ዝግ ከሆነ፤ ለድጋፍ አደራጊው ወይም የጥበቃ ሰራተኛው ያመልክቱ፡፡

የእርሶ ጤና-ነክ ጥያቄዎች እና ስለ በሽታዎ የተመዘገበ መረጃ በሚስጥር እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡

እንዲሁም በአደጋ ግዜ በመጀመሪያ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡  ለድንገተኛ አደጋ ብቻ ሲሆን በቀጥታ ወደ ሆስፒታል ይሂዱ፡፡

Icon_Medic_Help.png

እርሶ ወይም ልጅዎ ህመም ከተሰማችሁ እና ጤና ነክ ጥያቄ ካላችሁ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

 

የህክምና ድጋፍ በሌሎች የጥገኝነት መጠየቂያ ማዕከላት፡፡

በእያንዳንዱ የጥገኝነት መጠየቂያ ማዕከል ውስጥ ለጤና ነክ ጥያቄዎች የተወከሉ ግለሰቦች ይገኛሉ፡፡  ዝርዝር መረጃዎችን በቦታው ያገኛሉ፡፡