በሽታዎች

በበሽታ ለረጅም ግዜ እየተሰቃዩ ነበር? በየግዜው መድሀኒት ይወስዳሉ? በትውልድ አገርዎ ወይም በስደት ላይ እያሉ የህክምና እርዳታ አግኝተዋል?

Icon_Medic_Help.png

ወደ ሜዲክ ኸልፕ በመሄድ ችግሮትን ያብራሩ፡፡

አንዳንድ በሽታዎች ተላላፊ ናቸው፡፡  ይህ ማለት በሽታው ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ ይችላል፡፡  ይህም በአየር አማካኝነት፣ በቆሸሹ እጆች፣ በደም ወይም በወሲባዊ ግንኙነት እንዲሁም በማስመለስ፣ በሰውነት ፈሳሾች ወይም በቀጥታ ግንኙነት ሊከሰት ይችላል፡፡

Icon_Medic_Help.png

ምናልባት እነዚህ ምልክቶች ከታዩብዎ ከሜዲክ-ኸልፕ ጋር ይገናኙ፡፡ ይህም እርሶን እና በዙሪያዎ ያሉትን ሰዎች እንዲጠብቁ ይረዳል፡፡

እንደ ጎኖሪያ፣ ሲፍልስ ወይም ክላሚዲያ ያሉ በሽታዎች በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ ውጤቱ ሊያካትት የሚችላቸው ነገሮች ማዠት ፣ማሳከክ፣ መቁሰል ወይም በብልት አካባቢ ህመም መሰማት ናቸው፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት ምልክት ሳይኖርብዎ በበሽታው ተይዘው ሊሆንም ይችላል፡፡

Icon_Kondome.png

በግብረ ስጋ ግንኙነት ከሚተላለፉ በሽታዎች ራስዎን ይጠብቁ፡፡  በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ሁልግዜም ኮንዶም ይጠቀሙ፡፡ በማእከሉ ውስጥ ሊያገኟቸው ወይም ደግሞ ከኬሚስቶች ከፋርማሲ ወይም ከአብዛኞቹ ሱፐር ማርኬቶች ሊገዟቸው ይችላሉ፡፡

Icon_Medic_Help.png

ምናልባት የትኛውንም አይነት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የሚተላለፍ በሽታ ምልክት ካለብዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

Icon_Medic_Help.png

ካለ ኮንዶም ከተፈፀመ የግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ በግብረ ስጋ ግንኙነት ምክንያት በሚተላለፍ በሽታ ስለመያዝዎ እርግጠኛ ካልሆኑ ለማማከር ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡  ምልክት እስከሚያዩ ድረስ አይጠብቁ፡፡

ኤች አይቪ በሽታን የመከላከል አቅምን የሚያዳክም ቫይረስ ነው፡፡  ምንም አይነት ምልክት ሳያሳዩ ቫይረሱ በደምዎ ውስጥ ሊኖር ይችላል፡፡  መድሀኒት መውሰድ ካልጀመሩ ሰውነቶን ሊያዳክም ይችላል እስከ መታመም ደረጃ ሊያደርሶም ይችላል፡፡ ይህም ኤድስ ተብሎ ይጠራል፡፡ 

ይህ በሽታ የሚተላለፈው በደም፣ ያለ ኮንዶም በሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ ንፁህ ያልሆነ መርፌ በመጠቀም፣ ወይም ባልተወለደ ልጅ ላይ በቀጥታ ከእናት ወደ ልጅ ሊተላለፍ ይችላል፡፡  ይህ ቫይረስ ካለብዎ ምንም አይነት የበሽታ ምልክት ሳያሳዩ ወደ ሌሎች ሰዎችን ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡

ኤች አይቪ የሚድን በሽታ አይደለም፡፡  ነገር ግን መድሀኒቱ ቫይረሱን በመቆጣጠር እና ጉዳቱን በመቀነስ ያግዛል፡፡ 

Icon_Kondome.png

ራስዎን ከኤች አይቪ/ኤድስ ይጠብቁ፡፡ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ሁልግዜም ኮንዶም ይጠቀሙ፡፡ በማእከሉ ውስጥ ሊያገኟቸው ወይም ደግሞ ከኬሚስቶች፣ ከፋርማሲ ወይም ከአብዛኞቹ ሱፐርማርኬቶች ሊገዟቸው ይችላሉ፡፡

Icon_Spritze.png

በበሽታ መያዝን ለማስወገድ በደም ስር ለሚሰጡ መድሀኒቶች ሁልግዜም ንፁህ እና ጥቅም ላይ ያልዋለ መርፌ ይጠቀሙ፡፡

Icon_Medic_Help.png

ያለ ኮንዶም ከተፈፀመ የግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ በኤችአይቪ/ኤድስም ሆነ በሌላ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ መያዝዎን እርግጠኛ ካልሆኑ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ በመሄድ ይማከሩ፡፡   ምልክት እስከሚያዩ ድረስ አይጠብቁ፡፡

ቲቢ ያለባቸው ሰዎች ከሶስት ሳምንት በላይ ያስላሉ፣ ትኩሳት፣ የሌሊት ላብ ይኖራቸዋል፣ ወይም ክብደት ይቀንሳሉ፡፡  ቲቢ ጤነኛ የሆኑ ሰዎች ከህመሙ ጋር ያሉ ሰዎች ያሳሉበትን አየር ስበው ወደ ውስጥ ሲያስገቡ ሊተላለፍ ይችላል፡፡

ቲቢ አደገኛ ነው፡፡  ነገር ግን ይህ በሽታ በፍጥነት ከተደረሰበት ሊድን ይችላል፡፡  ህክምናው ቢያንስ ስድስት ወር ይፈጃል፡፡

Icon_Medic_Help.png

የትኛውም የቲቢ ምልክት ካለብዎ፣ ከዚህ ቀደም የቲቢ ህክምና አግኝተው ከነበረ፣ ወይም ከታመመ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ከነበርዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

አልኮል፣ መድሀኒቶች እና ሌሎች እፆች ሱስ ሊያስይዞት እና ጤናዎን ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ እፆችን መጠቀምን ያስወግዱ፡፡

በደም ስር የሚሰጡ እፆችን በምንጠቀምበት ወቅት መርፌ ስንጠቀም በሽታ የሚተላለፈው በደም ይሆናል፡፡

Icon_Spritze.png

እፁን መጠቀም ለማቆም ካልፈለጉ ሁልግዜም ንፁህ እና ጥቅም ላይ ውለው የማያውቁ መርፌዎችን ተጠቀሙ፡፡

Icon_Medic_Help.png

ሱሰኝነት ሊታከም እና ሊቀል ይችላል፡፡ ሜዲክ-ኸልፕን ያግኙ፡፡

በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፍ- እንደ ጦርነት፣ ማምለጥ፣ በሰዎች መሰቃየት እና መደፈር አካልን ወይም አዕምሮን ያሳምማል፡፡   በከፍተኛ መጠን አልኮል ወይም ሌላ አይነት እፅ መጠቀም በራሱ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡   

አብዛኞቹ የተጠቁ ግለሰቦች ስለ አዕምሮ ህመም ማውራት ከባድ ይሆንባቸዋል፡፡   ለሌላ በሽታ ትኩረት እንደምንሰጠው ሁሉ ለእነሱም ትኩረት መስጠት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ 

ሊሆን የሚችል የአዕምሮ ህመም ምልክቶች ውስጥ ለረዥም ግዜ እንቅልፍ ያለመተኛት፣ ቅዠቶች፣ እንግዳ የሆነ ህመም ወይም ሌሎች ችግሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

Icon_Medic_Help.png

የአዕምሮ ስቃይ ሊታከም ይችላል፡፡ ሜዲክ-ኸልፕን ያግኙ፡፡

ጉድፍ በጣም ተላላፊ የሆነ በሽታ ነው፡፡  ዋነኛ ምልክቶቹም ትኩሳት እና በቅድሚያ የቆዳ መቆጣት በግልፅ የሚታይ ክብ ማኮፍኮፍ ናቸው፡፡ ክትባት በመውሰድ ራስዎን ከጉድፍ መከላከል ይችላሉ፡፡

Icon_Medic_Help.png

እርሶ ወይም ልጅዎ የጉድፍ ምልክት ከታየባችሁ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

Icon_Medic_Help.png

እስከ አሁን ጉድፍ ይዞት የማያውቅ ከሆነ ክትባት ይውሰዱ፡፡  ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ

ኩፍኝ የያዛቸው ሰዎች በአብዛኛው በትኩሳት፣ በአይን መቅላት፣ በሳል እና በቆዳ መቆጣት በቀያይ ሽፍታዎች ይሰቃያሉ፡፡ ክትባት በመውሰድ እራስዎን ከኩፍኝ መከላከል ይችላሉ፡፡

Icon_Medic_Help.png

እርሶ ወይም ልጅዎ የኩፍኝ ምልክት ከታየብዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

Icon_Medic_Help.png

እስከ አሁን ኩፍኝ ከሌለብዎ ክትባት ይውሰዱ፡፡  ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ

ይህ ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ የላይኛው የመተንፈሻ ክፍል ወይም ቆዳ ህመም ነው፡፡ ሁለት አይነት ናቸው፡ የጉሮሮ እና የቆዳ ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ፡፡

በዚህ የጉሮሮ በሽታ የተያዙ ሰዎች በጉሮሮ ህመም፣ ትኩሳት እና በመዋጥ ግዜ ህመም ይሰቃያሉ፡፡  የዚህ ጉሮሮ ህመም በጣም ጠቃሚው ምልክት ለመዳን አስቸጋሪ የሆነ ቁስል ነው፡ ክትባት በመውሰድ ራስዎን ከተላላፊው የጉሮሮ በሽታ መከላከል ይችላሉ፡፡

Icon_Medic_Help.png

እርሶ ወይም ልጅዎ የዚህ ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ ምልክት ከታየብዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

Icon_Medic_Help.png

እስካሁን ይህ የጉሮሮ በሽታ ይዞት የማያውቅ ከሆነ ክትባቱን ይውሰዱ፡፡  ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ

ይህ በሽታ በጣም የተስፋፋ የቆዳ በሽታ ነው፡፡ ቆዳን ሰርስረው በሚገቡ ፓራሳይቶች አማካይነት የሚነሳ በሽታ ነው፡፡

ምልክቶቹም ከባድ ማሳከክ፣ ሽፍታ እና የቆዳ መቆጣት በአብዛኛው በብልት አካባቢ፣ በጣቶች መካከል፣ በእጅ አንጓ እና ሌሎች መገጣጠሚያዎች አካባቢ፣ በእጅ ስር እና በጡት ላይ ናቸው፡፡

ይህ በሽታ የሚተላለፈው በሁለት ሰዎች መካከል በቀጥታ የቆዳ ግንኙነት ሲኖር ነው፡፡

Icon_Medic_Help.png

እርሶ ወይም ልጅዎ የዚህ የቆዳ በሽታ ምልክት ካለብዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

ሆድ ውስጥ እና በአንጀት ውስጥ ማቃጠል ሲኖር፣ የማቅለሽለሽ ስሜት፣ ማስመለስ እና ተቅማጥ ከትኩሳት እና ከሆድ ውስጥ ህመም ጋር የሚከሰትበት ሁኔታ ነው፡፡ ይህ አይነት በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ግዜ በጣም ብዙ ፈሳሽ በአጭር ግዜ ያጣሉ፡፡

Icon_Medic_Help.png

ምናልባት የትኛውም አይነት የጨጓራ ህመም ምልክት ከታየብዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡

Icon_Trinken.png

በቂ ውሀ እና የተወሰነ መጠን ያለው ሻይ ይጠጡ፡፡

Icon_Haende_waschen.png

ሌሎችን መበከልን ለማስወገድ ሁልግዜም እጅዎን በሳሙና ይታጠቡ፡፡

ብዙ አይነት ሌላ በሽታዎች አሉ፡፡ እዚህ በዋነኛነት መረጃ የሚያገኙት በጣም አስፈላጊ ስለሆኑት በሽታዎች ብቻ ነው፡፡

Icon_Medic_Help.png

የበሽታ ምልክቶችዎ እዚህ ከተዘረዘሩት በሽታዎች ጋር የማይመሳሰል ቢሆንም እንኳ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡